ንስሓ እንዴት ልግባ?

በመጋቤ ምሥጢር አባ ኅሩይ ኤርምያስ “ንስሓ ግቡ” የሚለውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የዘወትር መልእክት ሰምተው አልያም በንስሓ ሕይወት የሚኖሩ መንፈሳውያንን አይተው በመንፈሳዊ ቅንዓት በመነሣሣት ወይም ደግሞ ያሳለፉት ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለበት በረከት አልባ የሕይወት ጉዞ አድክሟቸው ዕረፍትና ተስፋ በማጣት የዛለች ነፍሳቸውን ከእግዚአብሔር በሚገኝ ይርቅታ ከሥቃይ ለማሳረፍ በመሻት ብዙ ሰዎች ንስሓ መግባትን እየፈለጉ ንስሓ እንዴት እንደሚገባ ባለማወቅ ይቸገራሉ። […]