ንስሓ እንዴት ልግባ?

በመጋቤ ምሥጢር አባ ኅሩይ ኤርምያስ “ንስሓ ግቡ” የሚለውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የዘወትር መልእክት ሰምተው አልያም በንስሓ ሕይወት የሚኖሩ መንፈሳውያንን አይተው በመንፈሳዊ ቅንዓት በመነሣሣት ወይም ደግሞ ያሳለፉት ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለበት በረከት አልባ የሕይወት ጉዞ አድክሟቸው ዕረፍትና ተስፋ በማጣት የዛለች ነፍሳቸውን ከእግዚአብሔር በሚገኝ ይርቅታ ከሥቃይ ለማሳረፍ በመሻት ብዙ ሰዎች ንስሓ መግባትን እየፈለጉ ንስሓ እንዴት እንደሚገባ ባለማወቅ ይቸገራሉ። […]

ታላቅ የክብረ በዓል ጥሪ

የናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤና የቅዱሳን ምስጋና በብሩህ ደመና ወደ ሰማይ የማረጓን ክብረ በዓል በደብራችን በሐምቡርግ ደ/ መድኃኒት ቅድስት ኪደነ ምሕረት ቤ/ክ ከዋዜማው ቅዳሜ ነሐሴ 20 ቀን ከ 16:00 ሰዓት ጀምሮ እሁድ ነሐሴ 21 ቀን 2015 ዓ.ም (August 27/2023) ሊቃውንተ ቤ/ክ በተገኙበት በድምቀት ይከበራል ። እርሶም የዚህ ታላቅ በዓል በረከት ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም […]

በሐብቡርግ ደ/ መ/ ኪ/ ም ቤተ ክርስቲያን በደብሩ አስተዳዳሪ በመጋቤ ምሥጢር ዶ/ር አባ ኅሩይ ኤርምያስ ዐውደ ርእይ ኤግዚብሽን ተመርቆ ተከፈተ እንዲሁም ሌሎች አባቶችና የደብሪ ምዕመናን፣የሰንበት ተማራዎች፣ በተጨማሪም የተላያዩ የክብር እንዶች በተገኙበት ከጥቅምት 4 እስከ ጥቅምት 6 የሚቆይ ለዕይታ ቀረበ።

“ንዑ ርእዩ (መጥታችሁ እዩ !)”

ዐውደ ርእይ ኤግዚብሽን በሐብቡርግ ደ/ መ/ ኪ/ ም ቤተ ክርስቲያን በደብሩ አስተዳዳሪ በመጋቤ ምሥጢር ዶ/ር አባ ኅሩይ ኤርምያስ ዐውደ ርእይ ኤግዚብሽን ተመርቆ ተከፈተ እንዲሁም ሌሎች አባቶችና የደብሪ ምዕመናን፣የሰንበት ተማራዎች፣ በተጨማሪም የተላያዩ የክብር እንዶች በተገኙበት ከጥቅምት 4 እስከ ጥቅምት 6 የሚቆይ ለዕይታ ቀረበ።

አነ ውእቱ ገብርኤል ዘእቀውም ቅድመ እግዚአብሔር!

በመምህር ኅሩይ ኤርምያስ         ገብርኤል የሚለው ስም የሁለት ቃላት ጥምረት ነው ገብር አገልጋይ ፣ ባለሟል ማለት ሲሆን ኤል ደግሞ ስመ አምላክ ነው ስለዚህም ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ባለሟል ወይም አገልጋይ ማለት ነው። ልደተ ዮሐንስን ሊያበስር ወደ ዘካርያስ ተልኮ ሳለ ዘካርያስ ልጅ የማግኘት ተስፋው መንምኖበት ስለነበር የምስራቹን ቃል ለመቀበል በዘገየ ጊዜ የላኪውን ማንነት ቢያውቅ […]

“እስመ ኢየሱስ ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም ከመ ያድኅኖሙ ለኃጥአን … ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአተኞችን ሊያድን ወደ ዓለም መጥቷልና“ ፩ ጢሞ ፩፥፲፭

መጋቤ ምሥጢር ዶ/ር ኅሩይ ኤርምያስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።          ቸርነትና ይቅርታ የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ፥ ዓለማትን የፈጠረ ፥ ቀዳማዊና ደኃራዊ በአንድነቱ ምንታዌ በሦስትነቱ ርባዔ ሳይኖርበት እንደባለጸጋ በሀብት እንደ ነገሥታት በጉልበት እንደ ጣዖት በሐሰት ያይደለ ለንጽሐ ባሕርዩ ለጽንዐ አምልኮቱ በሚገባ እውነተኛ ምስጋና እርሱን ለማመስገን በሚተጉ በመላእክት ለአምልኮቱ በሚቀኑም […]

“አጽንዑ ቀዊመ በሃይማኖትክሙ – በሃይማኖታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ!“ ፩ ጴጥ ፭፥፱

መጋቤ ምሥጢር ዶ/ር ኅሩይ ኤርምያስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ምሕረትና ቸርነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ፥ ዓለማትን ፈጥሮ የሚገዛ ፥ ቀዳማዊና ደኃራዊ በአንድነቱ ምንታዌ በሦስትነቱ ርባዔ ሳይኖርበት እንደ ባለጸጋ በሀብት እንደ ነገሥታት በጉልበት እንደ ጣዖት በሐሰት ያይደለ ለጽንዐ አምልኮቱ በሚገባ እውነተኛ ምስጋና እርሱን ለማመስገን በሚተጉ በሰማያውያን መላእክት ለአምልኮቱ በሚቀኑም ምድራውያን ቅዱሳን አንደበት […]