አስተዳደር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛው አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ሲኾን እሱም በቤተ ክርስቲያኗ ጠቅላላ መንፈሳዊ አአስተዳደር ላይ ሥልጣን ያለው ነው። የሚመራውም በቅዱስ ፓትርያርኩ ኾኖ መንፈሳዊ ጉባኤውን በዓመት ሁለት ጊዜ ያደርጋል። በየአካባቢው ያለውን የቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በበላይነት የሚመራ “ሀገረ ስብከት” የተሰኘ አስተዳደራዊ መዋቅር ሲኖር ሊቀ ጳጳሱ የሀገረ ስብከቱን የአስተዳደር ጉባኤ በሊቀ መንበርነት ይመራሉ። በዓመት አንድ ጊዜ […]

ዝማሬ እና ሥነ ጥበብ

የዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና ሕይወትና በጠቅላላው በመንፈሳዊ ባሕሉ ላይ አዲስ ምዕራፍን ከፍቷል። ዝማሬና ኪነጥበብ በእጅጉ ተስፋፍቷል። ለዚህም ዋና ምሳሌ ኾኖ የሚጠቀሰው በታዋቂው የአክሱም ሊቅ በነበረው በቅዱስ ያሬድ የተደረሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ድርሰት ነው። ቅዱስ ያሬድ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የነበሩት የአባ አረጋዊ ደቀመዝሙር ነበር። እሱም እስካሁን […]

መንፈሳዊ አገልግሎት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ አገልግሎቶች ይሰጣሉ። የመጀመሪያው በቤተ መቅደስ በካህናትና በዲያቆናት አማካኝነት የሚከናወነው የቅዳሴ ሥርዓት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በመዘምራንና በሊቃውንት የሚሰጠው የማሕሌት፣ የሰዓታት፣ የፍትሐት፣ ወዘተ. አገልግሎት ነው። በቤተ ክርስቲያኗ በሚሰጡ አገልግሎቶች ምእመናን ከፍተኛ ተሳትፎ ያደርጋሉ። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜ በአጽዋማት እና በክብረ በዓላት ይለያያል። በጾም ጊዜያት ቅዳሴ የሚጀመረው ከቀኑ በ7 ሰዓት ነው። […]

አጽዋማት እና በዓላት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 7 የአዋጅ አጽዋማት ጊዜያት አሏት። እነዚህም፣ 1. ረቡዕ እና ዓርብ (ከበዓለ ሃምሳ ማለትም ከትንሣኤ በኋላ ካሉት 50 ቀናት በስተቀር)፣ 2. ዐብይ ጾም፣ 3. የነነዌ ጾም፣ 4. ጾመ ገሃድ (የጥምቀት ዋዜማ)፣ 5. ጾመ ሐዋርያት፣ 6. ጾመ ነብያት፣ እና 7. ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ናቸው። ቤተ ክርስቲያኗ አምላክን እና ቅዱሳኑን የምታከብርባቸው በርካታ በዓላት […]

መሠረተ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት አባል እንደመሆኗ መጠን እነሱ የሚከተሉትን መሠረተ እምነትና ቀኖና ትቀበላለች። ይህ መሠረተ እምነቷ በብሉይ ኪዳን መሠረትነት፣ ከሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ የሐዲስ ኪዳን መሠረተ እምነት ነው። ይህም ከጥንት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኗ አባቶች እና በመምህራን ሲሰበክ የኖረ እምነት፣ አሁንም ያለ፣ ወደፊትም ሕያው ሆኖ የሚኖር ነው። በአጭር ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ […]

ታሪክ

ኢትዮጵያ የክርስትናን እምነት የተቀበለችው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ሐዋርያው ፊልጶስ ባጠመቀው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አማካኝነት ነበር። ክርስትና በሀገሪቱ ይስፋፋ ዘንድ ፈጻሚና አስፈጻሚ የሆነችው ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በ328 ዓ.ም. ብሔራዊት ሆና ሲኖዶሷን መሠረተች።  የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረት በዚህ መልክ በሀገሪቱ ይተከል ዘንድ አስተዋጽዖ ያደረገው አባ ፍሬምናጦስ የተባሉት በትውልድ ሶርያዊ የሆኑ ነገር ግን በአክሱም ቤተ […]