አጽዋማት እና በዓላት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 7 የአዋጅ አጽዋማት ጊዜያት አሏት። እነዚህም፣ 1. ረቡዕ እና ዓርብ (ከበዓለ ሃምሳ ማለትም ከትንሣኤ በኋላ ካሉት 50 ቀናት በስተቀር)፣ 2. ዐብይ ጾም፣ 3. የነነዌ ጾም፣ 4. ጾመ ገሃድ (የጥምቀት ዋዜማ)፣ 5. ጾመ ሐዋርያት፣ 6. ጾመ ነብያት፣ እና 7. ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ናቸው። ቤተ ክርስቲያኗ አምላክን እና ቅዱሳኑን የምታከብርባቸው በርካታ በዓላት አሏት። ከነዚህም ውስጥ ዋናዎቹ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደትና የማዳን ሥራ የምናዘክርባቸው 9 ዐበይትና 9 ንዑሳን በዓላት ናቸው። በተጨማሪም ለቅዱሳንና ለመላእክት መታሰቢያ የሚከበሩ ሌሎች በዓላት አሉ።