ዝማሬ እና ሥነ ጥበብ

የዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና ሕይወትና በጠቅላላው በመንፈሳዊ ባሕሉ ላይ አዲስ ምዕራፍን ከፍቷል። ዝማሬና ኪነጥበብ በእጅጉ ተስፋፍቷል። ለዚህም ዋና ምሳሌ ኾኖ የሚጠቀሰው በታዋቂው የአክሱም ሊቅ በነበረው በቅዱስ ያሬድ የተደረሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ ድርሰት ነው። ቅዱስ ያሬድ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የነበሩት የአባ አረጋዊ ደቀመዝሙር ነበር። እሱም እስካሁን ድረስ በቤተክርስቲያን የሚታወቁትን ሦስት የዜማ ዓይነቶች (ግዕዝ፣ እዝል እና አራራይ) ደራሲና አቀናባሪ መንፈሳዊያት የዜማ ድርሰቶች የሚመስጡ ናቸው። ይህ መፈሳዊ በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ነው። እነዚህ ስሜትን እጅግ የዜማ ድርሰትም ካሉት ዜማዎች የዘጠኙ ቅዱሳን በዓይነቱ እጅግ የተለየ ነው። ስብከተና ትምህርትም የሥነ ጽሑፍ እና የሥነ ሕንፃ ዕውቀት እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል። በአክሱም፣ በአዱሊስ፣ እና በሐውልቲ ከተሞች የሚገኙ ጥንታዊ ፍርስራሽ ሕንፃዎች ከሶሪያ አብያተ ክርስቲያናት ሥነ ሕንፃ ጋር ተመሳሳይነት ይታይባቸዋል። ሌላው እና ታዋቂው የደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም እስካሁን ከሚታዩት እጅግ ጥንታዊ ከኾኑት የክርስትና የሥነ ሕንፃ ጥበብ ሥራዎች አንዱና ዋነኛው ምሳሌ ነው።