መሠረተ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት አባል እንደመሆኗ መጠን እነሱ የሚከተሉትን መሠረተ እምነትና ቀኖና ትቀበላለች። ይህ መሠረተ እምነቷ በብሉይ ኪዳን መሠረትነት፣ ከሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ የሐዲስ ኪዳን መሠረተ እምነት ነው። ይህም ከጥንት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኗ አባቶች እና በመምህራን ሲሰበክ የኖረ እምነት፣ አሁንም ያለ፣ ወደፊትም ሕያው ሆኖ የሚኖር ነው። በአጭር ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ ታሪካዊ የክርስትና እምነትን ለዘመናት ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ ያቆዩ አባቶች እና ምእመናን ተቋም ናት።