አጽዋማት እና በዓላት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 7 የአዋጅ አጽዋማት ጊዜያት አሏት። እነዚህም፣ 1. ረቡዕ እና ዓርብ (ከበዓለ ሃምሳ ማለትም ከትንሣኤ በኋላ ካሉት 50 ቀናት በስተቀር)፣ 2. ዐብይ ጾም፣ 3. የነነዌ ጾም፣ 4. ጾመ ገሃድ (የጥምቀት ዋዜማ)፣ 5. ጾመ ሐዋርያት፣ 6. ጾመ ነብያት፣ እና 7. ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ናቸው። ቤተ ክርስቲያኗ አምላክን እና ቅዱሳኑን የምታከብርባቸው በርካታ በዓላት […]

መሠረተ እምነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት አባል እንደመሆኗ መጠን እነሱ የሚከተሉትን መሠረተ እምነትና ቀኖና ትቀበላለች። ይህ መሠረተ እምነቷ በብሉይ ኪዳን መሠረትነት፣ ከሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ የሐዲስ ኪዳን መሠረተ እምነት ነው። ይህም ከጥንት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኗ አባቶች እና በመምህራን ሲሰበክ የኖረ እምነት፣ አሁንም ያለ፣ ወደፊትም ሕያው ሆኖ የሚኖር ነው። በአጭር ቃል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ […]

ታሪክ

ኢትዮጵያ የክርስትናን እምነት የተቀበለችው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ሐዋርያው ፊልጶስ ባጠመቀው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አማካኝነት ነበር። ክርስትና በሀገሪቱ ይስፋፋ ዘንድ ፈጻሚና አስፈጻሚ የሆነችው ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በ328 ዓ.ም. ብሔራዊት ሆና ሲኖዶሷን መሠረተች።  የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረት በዚህ መልክ በሀገሪቱ ይተከል ዘንድ አስተዋጽዖ ያደረገው አባ ፍሬምናጦስ የተባሉት በትውልድ ሶርያዊ የሆኑ ነገር ግን በአክሱም ቤተ […]

የሥርዓተ ቅዳሴ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ፕሮግራሞች

የጊዜ ሰሌዳ ከ ጥር 2012 እስከ ታኅሣሥ 2013 ዓ/ም (Januar 2020 – Dezember 2020) የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሐምቡርግ ደብረ መድኃኒት ኪዳነ ምሕረት የሥርዓተ ቅዳሴና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በሚከተሉት ጊዜያት የሚደረጉ መሆናቸውን በአክብሮት እናሳውቃለን። ቦታ Wehrmannstraße 7-9 , 21109 Hamburg ሥርዓተ ቅዳሴ Gottesdienst 06.01.2020 20:00 ሰዓት Uhr 12.01.2020 07:00 ሰዓት Uhr 26.01.2020 07:00 ሰዓት […]